በተቃውሞው ሰፈር ዉስጥ አንዳንድ ወገኖች ከወያኔ በበለጠ ሁኔታ ደግመው ደጋመው ሊያሳምኑን የሚፈልጉት ጉዳይ የዲሞክራሲ ጭላንጭል እና ጠባብም ቢሆን ምህዳር መኖሩን ነው።በተጨማሪም ይህ ጪላንጪል እና ምህዳር ደብዛው እንዳይጠፋ "ህገመንግስታዊ " መብታቺንን ተጠቅመን ልናድነው ይገባል በማለት ካለፉት ሁለት አስርት አመታት ወዲህ ጀምረው በግልጽ እና በሚያሳምን መልክ ይቀሰቅሳሉ፤በየመድረኩም የከራከራሉ።
ሃቁን እንመልከተው ከተባለ ግን በእርግጥ ዴሞክራሲ አለን?ምህዳርስ ይኖራልን?አንድ ጠባብ ጎሰኛ ቡድን ድርጂትም፤መንግስትም፤ሁሉን አቀፍ ተቁዋም በሆንበት ሁኔታ ምን አይነት ዴሞክራሲና ምን አይነት ምህዳርስ መጠበቅ ይቻላል?የራሱን ህጎች እና ድንጋጌወች ብቻ ስይሆን ህገመንግስት እየተባለ የሚመጻደቁበትን ሰነድ በግልጽ እና በእዳባባይ ደግሞ ደጋግሞ የጣሰና አምባገነንነቱን በገሃድ ካረጋገጠ ማፍያዊ ቡድን ከአፈና በስተቀር ምንስ ይጠበቃል? እነዚህ ስለዴሞክራሲና ምህዳር እጃቺንን ጠምዝዘው ሊግቱን የሚፈልጉ ወገኖች ለመሆኑ ስለዲሞክራሲና ምህዳር ጠቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ ይኖር ይሆን ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው።ምክንያቱም ህዝቡን ማወናበድ እና ተቃዋሚዉንም መከፋፈል አይነተኛ ስራቸው መሆኑን ለማወቅ እነዚህን ጥያቄወች ማንሳትና ፊት ለፊት መጋፈጥ ወቅቱ የሚጠይቀው የሁላቺንም ግዳጅ ነው።
የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር እና ከወያኔም አደገኛ ፖሊሲወች የመታደጉ ተግባር እያደር ዉስብስብ እንዲሆን ካስገደዱት ጉዳዮች አንዱ በተቃውሞው ሰፈር በየጊዜው የሚፈጠረው ብዥታ እና የጋራ ግንዛቤ እጥረት ነው።
ስልጣን ላይ ያለው ወያኔም ይህን ድክመት ጠንቅቆ ያወቀ ይመስላል በህቡእ እያደራጀ በኢትዮጵያ የሚምሉና የሚገዘቱ አወናባጆቺን መካከላቺን ያሰማራቸዋል።ስለዚህም ነው ዛሬ በህዝባቺን እና በተቃዋሚዉም ሰፈር ስለዴሞክራሲ-ህገመንግስት-ምህዳር-ጭላንጭል መኖር ያለመታከት የሚቀሰቅሱን እየበረከቱ የመጡት።ዴሞክራሲ ተብየው ፋቅ ፋቅ ሲደረግ የለየለት አምባገነንነት እንደሚሆነው ሁሉ የምህዳር ቀስቃሾቺም ፋቅ ፋቅ ቢደረጉ ወያኔ ሆነው ነው የምናገኛቸው።
እነዚህ የምህዳር-ዴምክራሲ ካድሬወች ከወያኔ በተሰጣቸው ስዉር መመርያ መሰረት በመጀመርያ ድል የጠማዉን ህዝብ በመሃል አገር መድረክ ላይ እየተውረገረጉ-ዉሎ አበል እየተከፈላችዉና የሜዲያ ሽፋን እየተሰጣቸው "ምህዳሩ" እንዲሰፋላቸው ወያኔን መማጸን እንደሚገባ ሲሰብኩና ሲያወናብዱ ነው የከረሙት። ዛሬ ደግሞ በዴያስፖራው መካከል ያንኑ የለመዱትን የማወናበድ ስራ የቀጠሉ ቢመስልም መንገዱ አልጋ ባልጋ አልሆነላቸዉም።ባንዳንድ ቦታም አዳማጪም አላገኙ።የቅስቀሳቸዉና የመልእክታቸው ፍሬነገር ሲመነዘር የወያኔን ድብቅ አጀንዳወች ያነገበ መሆኑን ሁሉም ስለሚያዉቅ "ወተሃወጹ-በከንቱ!!" ብሎ ሸኝቶዋቸዋል።ዴያስፖራዉን በተደጋጋሚ ሊቆጣጠር የሜመኘው ወያኔ በልዩ ልዩ መንገድ ሙከራ ቢያደርግም ከእንግዲህ እንደማይሳካለት ለማረጋገጥ ግን በቂ ትምህርት ያገኘ ይመስላል።
በዚህ ጉዳይ እጂግ የሚያሳዝነዉንና የሚገርመዉን ሁኔታ አለማንሳት ለዘብተኝነት ወይም ወንጀል ነው ብለን ስለምናምን መጥቀሱን እንወዳለን። እነዚህ የምህዳር-ዴምክራሲ ካድሬወች ከየት ተነስተው የት ደረሱ?እነማንስ ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው እዚህ ደረሱ?ዛሬስ እነማን ናቸው እንኮኮ ብለው የተሸከሙዋቸው?እነማንስ ናቸው ጋሻ ጃግሬ በመሆን ሃቀኛ ጸረ-ወያኔ ትግሉን እየከፋፈሉና እየደቆሱት ያሉት?እነማንኛቸው ዛሬ እነስዬን የኢትዮጵያ ባንዲራ አልባሽና ጃንጥላ ያዥ ሆነው እስክስታ የሚወርዱላቸው?እነዚህ ጥያቄወች የወያኔን ጠባይና አሰራር ላወቀ ሁሉ መልስ ማግኘት አይከብደዉም።መጠፍጠፍና ማሰማራት ብቻ ሳይሆን ድርጂቶቺንም በራሱ ሰላዮች እየቦረቦረ ሰርጎ መግባት መደበኛ ስራው የሆነው ወያኔ በህጋዊ መንገድ የተቁዋቁዋሙትን ታማኝ ድርጂት ተብየወች ተጠቅሞባቸዋል፤እየተጠቀመባቸዉም ነው። ይህ ሁኔታ ግልጽ መሆን እና መታወቅ አለበት።ወዳጅ ጠላት በግልጽ ይወቀው።ለምን ተነካን የሚሉም ለይቶላቸው እንደፍርጥርጣቸው ይሁኑ።ባለፉት 21 አመታት ታማኝ ተቃዋሚ መሆን እና የወያኔ ጪዳ መሆን አንድ ከመሆኑ ሌላ ለወያኔ መጠቀምያ በመሆንም አደገኛ ሴራ ማጠንጠኛ በመሆንም በመድረክነት እያገለገሉ ነው።ይህ መታወቅ ያለበትና ህዝቡም እንዲያውቀው ተብጠርጥሮ ሊቀርብለት ይገባል።ታማኝ ተቃዋሚወች እነማን ናቸው?ምን እየሰሩ ነው?ማንን እያገለገሉ ነው?አላማቸው ምንድን ነው?ትግሉን በምን መልክ እየገደሉት ነው?አገራቺንን በምን እና ምን መልክ እየጎዱዋት ነው?መፍትሄዉና መከላከያው ምንድንነው?እና የወያኔ ህቡእ ካድሬወች ባንዲራቺንን እየለበሱ--ስለኢትዮጵያ አንድነት ጆሮዋቺንን እስኪያመን ድረስ ሊነግሩን አይገባቸዉም፤ጥንቱኑ ከመነሻው አሳምረው በገደሉት ዴሞክራሲ አመካኝተዉም ምህዳሩን እናስፋው በማለት ማንንም ከእንግዲህ ሊያጃጅሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም!!!ወጣቶች ሰሞኑን በነስዬ ላይ የሰነዘሩት የማጥቃት እርምጃ ሊጎለብትና በየሄዱበት ሊከተላቸው የሚገባ በጎ ጂምር ነው።
እናት ኢትዮጵያ የወላድ መካን ትመስል እጃቸው በህዝብ ደም የተጨማለቀውና በአፋኝነት እውቅና የተሰጠዉን ገዳይ ስርአት ሲመሩና ሲያቀነባብሩ የነበሩ ሰወች ዛሬ አርበኛ እና ነብይ ተብለው ከህዝቡ ፊት እንዲቀርቡ ማመቻቸት ታላቅ ወንጀል ነው።ሜዲያ እየተሰጣቸውም ያኑን ወንጀላቸውን እንዲከላከሉ ብቻ ሳይሆን ሃገሪቱ ያል እነሱ የሚታደጋት እንደሌለ አስመስሎ ማቅረብ ጸያፍ ነው፤ህዝብንም መናቅ ነው።ድርጊቱንም በለዘብተኝነት ማየት የወንጀል ተባባሪነት ነው።መድረክ ተብሎ የሚታወቀው አስመሳይ የወያኔ ዋሻ እንዲህ አይነት መቀለጃና መረማመጃ ሆኖ በህግ ተመዝግቦ መገኘቱ በህዝባቺን ላይ የሚደርሰው አፈና እና ረገጣ የትየለሌ መሆኑን ነው የሚያረጋግጠው።መድረክ ወያኔን እንዲያገለግል እና የተቃዋሚዉን ስፈር ለመሰለል ተብሎ የተመቻቸ ነው።ኢትዮጵያዊ መስሎ ለመቅረብ፤ወያኔንም መቃወም ለመልመድ፤በዲያስፖራ ካሉ አስመሳዮች ወይም የወያኔ ትክለኞች ጋር ግንኙነት ለመመስረት፤በመጨረሻም ወያኔን በጽናት የሚታገለዉን ሃይል ቦርቡሮ ለመግባት እና ለመከፋፈል ተጠቅመዉበታል--እየተሳካላቸዉም ይመስላል--ትግሉ እየተጉዋተተ 21 መቱን እየቆጠረ ነው።ወያኔ በሃቀኛ ወገኖች ላይ በግልጽ ከሚያደርሰው ጥቃት ይልቅ በመድረክና በመሳሰሉት ሰርጎገቦች የሚደርሰው ጥቃት ሃያል እና ከባድ በመሆን ላይ ነው።
እነመድረክ ተብየወች ሕዝባቺንን በግላጪና በአደባባይ ስላገኛቸዉ ብቻ ሙሉ እመንቱን እና ይሁንታዉን እንደሰጣቸው አድርገው ሊነዱት ሞክረዋል።የህወሃትን የጪቆና መዋቅሮችና አዋጆች አሜን ብሎ እንዲቀበል ገፍተዉታል።ህገመንግስት ስላለ ህገመንግስታዊ መብቱን እንዲያስከብር ቀስቅሰዉታል።ወያኔ ህዝባዊም ዴሞክራሲያዊም ነው በሚል ያለሃፍረት አስተምረዋል።ህዝቡን በጠላቶቹ ፊት እንዲጎናበስና እንዲንበረከክ መክረዉታል።ወዳጂና ጠላቱንም መለየት እስኪያቅተው ድረስ አወናብደዉታል።ህዝቡ ወጊዱልኝ ብሊቸዉም በወያኔ ረዣዥም እጆች እና የፋይናንስ ድጎማወች ከወደቁበት እየተነሱ ያንኑ የማወናበድና የመከፋፈል ስራቸዉን ቀጥለዋል።አድርባይነትን እና ተንበርካኪነትን ለወጣቱ አሳይተዋል።ለመብት መታገልንና መስዋእት መሆንን አኮላሽተዋል።በጋዜጣዊ መግለጫና በጥቂት ጽሁፎች ብቻ ስርአቱ ይወድቅ ይመስል ደካማነትን እና ነፈዝነትን በወጣቱ መካከል አስርጸዋል።ሃቀኛዉን የህዝብ ትግል በሚመሩ እና በሚያደራጁ ላይ ከወያኔ ጎን ቆመው ኮንነዋል።በሰላዪነትና በጆሮጠቢነትም እያገለገሉ ነው።"ለመለስ ዜናዊ ራእይ" ህዝቡን አሰልፈዋል፤የሃዘን ተካፋይነታቸዉንም አረጋግጠዋል፤መንታ ሴራ እያሴሩ ሲሆን ለወያኔም አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጡ ነው።በቃ! የሚለው መፈክር ለዚህ አስቀያሚ ሁኔታ ተስማሚ ነው።
በሌለ ዴሞክራሲ ሊኖር የማይችል ምህዳር መናፈቅ የፖለቲካ ቂልነት ብቻ ሳይሆን ድብቅ አላማ ማራመጃም ነው።ቀድሞዉኑ ዴሞክራሲ ሲኖር የማስፋፋት እና የማበልጸግ እድል እና ህልም ሊኖር ይቺላል። በአንጻሩ ዴሞክራሲ ሳይኖር ምህዳር እያሉ መድረቅ አሁንም የፖለቲካ ጂልነት እንጂ መፍትሄ አይደለም።እንዲያዉም ምህዳር እያሉ ህዝብን ማደንቆር ወያኔን እጂ-መንሳት እንደማስተማር ከመቆጠሩ ሌላ ከወያኔ ጋር መሞዳሞድን የሚያስተምር መቅሰፍታዊ-አስተሳሰብ ነው።ወያኔ አገር አጥፊ እና ወንጀለኛ እንጂ ዲሞክራሲን እና ምህዳር ለተቃዋሚወቹ እንኩ ብሎ የማያውቅ መሆኑን ሪከርዱ እያሳየ ዛሬም ከስንት አመታት በሁዋላ እነታጋይ ስዬ ምህዳሩን ለማስፋት ህገመንግስታዊ መብታቺንን እንጠቀም ማለቱ ከወንጀልም በላይ ታላቅ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።ከሁሉ በላይ የወያኔ ብቻ ሳይሆን ከመሃሉ ወጣን እያሉ ሊያጃጅሉን የሚሞክሩትን- ጆሮ እንድንሰጥ እና የነብይነት ቺሎታቸዉን እንድናደንቅ የሚጋብዙንን "መድረኮች" እርቃናቸዉን ማስቀረትና ከእንዲህ አይነት ጸር-አንድነትና ጸረ-ኢትዮጵያ ድርጊት እንዲታቀቡ ማድረግ የወቅቱ ግዳጅ ይሆናል።እንዲህ አይነቶቺን አስመሳዮቺና ትግል-አምካኞች ድል ሳያደርጉ ወያኔን ከነግሳንግሱ መገርሰስ አይቻልም።ከመካከላቺን በተቃውሞ ስም--በኢትዮጵያ ስም--በአርበኝነት ስም-በታጋይነት ስም-በጸረ-ወያኔነት ስም የተቀላቀሉንን ማግለልና ማጽዳት የወቅቱ ግዳጅ ነው።እሾህና አሜኬላዉን በጉያ ሸጉጦ ኢትዮጵያን ማዳን ከንቱ የከንቱም ከንቱ ነው።ትግሉና ሂደቱ መጽዳት አለበት።እናት ኢትዮጵያ የወላድ መካን አይደለቺም።
No comments:
Post a Comment