Sunday, 30 January 2011

ነዳማ ለማን እና ለምን!!!

        ይህ ነፃ የሆነ አስተያየት የሚሰጥበት እና በፌስ ቡክ ላይ የሚወጡ የፕሮፓጋንዳ ስራወችን የሚያግዝ ሃተታ ነው.ከማንኛዉም  የፖለቲካ ድርጅት ነፃ የሆነ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት እና ትችት የሚያቀርብ አምድ ነው.

        የታጋይ ህዝባዊ ድርጂቶችን እና የፓለቲካ ፓርቲወችን እንቅስቃሴ እና መግለጫወችን እናቀርባለን-እናስተዋውቃለን-ሂስና ድጋፍም እንሰጥበታለን:: ባንዳዉንሆዳሙን-አጎብዳጁን-እርምጥምጡን-እሾህ አሜኬላዉን መንጥረን እንተቸዋለን::

        ነዳማ! ይህ ቃል አጼ ህይለስላሴን እና የጸጥታ ካቢኔያቸዉን እንዲሁም በመጨረሻ ዋለልኝ መኮንን እና አጼዉን ያፋጠጠ የፖለቲካ ቃል ሆኖ አገልግሎዋል።እናም ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ህዋ ገብቶ ስራ ላይ የዋለው የዛሬ አርባ አመት ግድም በገናናው የኢትዮጵያ ተማሪወች እንቅስቃሴ ወቅት ነው።ወደ ፖለቲካ መድረኩም ብቅ አድርጎ ከአጼው ስርአት ጋር የተፋጠጠበት ዋለልኝ መኮንን የተባለው የተማሪወች መሪ ነበር።

            ነዳማ ምንጩ አማርኛ ሲሆን በይበልጥ የሚነገረው በሰሜን ኢትዮጵያ ነው.ጸጸት-የህሊና ወቀሳ እንደማለት ሲሆን ያለፉ ስህተቶችን እንደትምህርት ወስዶ በወደፊቱ ላይ የሚያነጣጥር ሃገር በቀል ፍልስፍና ነው.

         ነዳማ የራስን ህሊና መግዛት እና ማረም መቻል ይሁን  እንጂ ከፖለቲካው ጋር ሲወሰድ ሰፊ ትምህርት የሚገኝበት እና የሚቀሰምበት የአስተሳሰብ ልጉዋም ነው.

         ነዳማ በአለፈው ዉስጥ የወደፊቱን አሻግሮ የማየት ቺሎታ ሲሆን መጭዉን ከዉድቀት እና ከድክመት በማዳን ለስኬት የሚያበቃ የአማርኛ ይትበሃል ነው.

          ስለዚህ እኛም ነዳማ በማለት ያለፉትን ሂደቶች እና ክስተቶች በመገምገም ለአገራቺን እና ለህዝባቺን የሚጠቅመዉን ለማመላከት የበኩላችንን አንድ እንላለን.

እንዲያዉም...........

               ኢትዮጵያን የማዳኑ ጉዳይ የጥቂቶች የቤት ስራ ነው ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው!!ስለዚህም ወቅቱ በልማት-በዲሞክራሲና-በሰላም ስም ወያኔ እየገፋው ያለው ሃሳብ እና ዘዴ ሁሉ አገሪቱ እንደ አገር--ህዝቡም እንደህዝብ እንዳይቀጥል የሚያመቻች  መሆኑን አምኖ መቀበል ግድ ይላል::

             ከዚህም በላይ ወያኔን እንደልማትና ዴሞክራሲ ሃይል የማየቱ ዝንባሌና  እና አዝማሚያ ቸል የማይባል አደገኛ አመለካከት በመሆኑ ልንዋጋዉና ልናጋልጠው የሚገባ  ወሳኝ  የፓለቲካ  ስራ ነው ብለን እናምናለን::

            የወያኔ የፓለቲካና የፕሮፓጋንዳ መጠነ-ሰፊ ዘመቻ ለአገራችን መዳከም እና ለአድርባይነት መስፈን ታላቁን አስተዋጾ ያበረከተ በመሆኑ ነዳማ ይህን የመመከት ባህል ለማዳበር የበኩሉን ድርሻ ይጫወታል::


      ነዳማን ስንመሰርት በአእምሮዋችን ሲጉላሉ የነበሩ በርካታ ጉዳዮች ነበሩ። ጥቂቱ፤

------የፖለቲካ ጉዳዮቺን ለጋዜጠኞች እና ለሜዲያ ሰወች መተው አለብን?

                                      ወይስ

-----ተስፋቺንን፤ቅሬታችንን እና ተቃውሟቺንን

ለማስማት ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል አይገድበንም ብለን እነነሳ?

መልሱ አጪር እና ግልጽ ነበር።

                ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም በያለበት-በየፊናው- ባመቸው መንገድ ይታገል!!!!!


                 ነገርግን አንድ ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት::ኢትዮጵያን ማዳን አሮጌዉን ስርአት እንደማዳን መቆጠር የለበትም::

               ኢትዮጵያን ማዳን ስንል አምባገነኖችን እና አገር አጥፊወችን  መልሰን ስልጣን ለማከፋፈል አይደለም!!

              ኢትዮጵያን ማዳን ስንል አገራችንን እና ህዝባችንን ለውድቀት ያበቁ  ፓሊሲወች-የከሰሩ መፍትሄወች-አጥፊ አካሄዶች ነፍስ ዘርተው እንደገና ወደ ጥፋት መጉዋዝ አይደለም!!


         ኢትዮጵያን ማዳን ስንል ሁሉም አይነት ጸረ-ኢትዮጵያ እና ጸረ-አንድነት ሃይሎችን አበጃቺሁ-እሰየው ብለን ልንሽልማቸዉና ልናሞግሳቸው አይደለም!!


                 ኢትዮጵያን ማዳን ስንል አሮጌ ሃሳቦችን እና መፍትሄወችን ወደጎን ሽኝተን በወጣቱና ዲሞክራሲያዊው ሃይል አማካኝነት ህዝቡን በቀጥታ ያገሩና የስልጣኑ ባለቤት ማድረግ ማለት ነው!!

                ስለዚህ ነው ነዳማን ከሌሎች የፕሮፓጋንዳ ስራወች ጋር ጎን ለጎን  እንድትሄድ ስናመቻቻት ቆይተን እነሆ አንድ አመትዋን ቆጥራ ብቅ እንድትል ያበቃናት!!!!


              በፖለቲካ ድርጂቶች እና ንቅናቄወች እንዲሁም በሃገራቺን የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ሚና ባላቸው ሃይሎች ላይ ትሳተፋለች።  ነዳማ!!!!! ብለናል----የኢትዮጵያ ጉዳይ ለጥቂቶች ብቻ የሚተው እንዳልሆነም አረጋግጠናል!!!!!
 

ወያኔን መታገል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዳጅ ነው!!
ካልተደራጀ ኢትዮጵያዊ የለየለት ወያኔ "ይሻላል"!!

 ጥር 2003

No comments:

Post a Comment