ሕወሃት /ወያኔ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወጥቶ መሃል አገር የፈነዳ ትኩስ "ዴሞክራት" በመሆኑ የማይችለበትን እና የማያውቅበትን የሃገር እና የህዝብ አስተዳደር ቀዉስ ዉስጥ እንደጣለው በገሃድ የታየ ነው::የጎጥ መርሆዎቹን ከአገራዊ ፍላጎቶች ጋር--አገራዊ ፍላጎቶቹን ደግሞ ከአለም አቀፋዊ ጉዳዮች ጋር ማጋመድ ስላልቻለበት ላለፉት ሃያ መናምን አመታት አገሪቱን የእዉር የድንብሩን ሲያተራምሳት እንጂ በወጉ ሲያስተዳድራት አልነበረም::
ወያኔ መነሻዉና መንደርደርያው ጎጡ እና ጎጡ ብቻ ስለሆነ የተቃና ሁሉን አቀፍ የህዝብ አስተዳደር እና አመራር ፓሊሲ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ነው::ባገሪቱ ነባር ባህላዊ መዋቅሮችም ይሁን እነሱው በጠፈጠፉዋቸው መዋቅራት ዉስጥ አለም ያወቃቸዉን የአስተዳደር ስርአቶችን ወድጎን በመግፋት ወታደራዊ ስልቶችን በሲቭል መስርያቤቶች ሳይቀር ተጠቅመዋል::
ወያኔ ህዝቡን በረዥም ታሪኩ ባዳበረዉና እና ባበለጸጋቸው የአስተዳደር ዘዴወች መምራትእንዳልቻሉበትና ይልቁንስ ደግሞ ደጋግሞ ከህዝብ ጋር እየተጋጩ እንደሆነ በርካታ ማስረጃወችን መደርደር ይቻላል::በደቡብ ያገሪቱ ክልሎች የራሱን ህገመንግስት ጥሶ የአናሳ ብሄር ብሄርሰቦችን መብት እና ህልዉና ሲጨፈልቅ እንደነበር በ2004/5 በሪፓርት ተመዝግቦ አንብበናል:በ አለም አቀፍ የዜና አውታሮች እና ሰብ አዊ መብት ተንከባባካቢ ወገኖችም አማካኝነት አለም እንዲሰማው ተደርጎዋል::::
እንዲያው ለመነሻ ያህል ወያኔና የህዝብ አገልግሎት ፓሊሲወች ጭራሽ እንደማይተዋወቁ --በዚህም ሳብያ ማህበረሰቡ በበርካታ ወያኔ ሰራሽ ቀውሶችና ውጥረቶች የተቀፈደደ መሆኑን ከጠቆምን በሁዋላ በያመቱ ከወጣቱ ጋር የሚያደርገው ትንቅንቅ ዘንድሮ ምን ሊመስል ይችላል:-ወጣቱስ ምን ምርጫ አለው በማለት በጥቂቱ ለመዳሰስ ነው ይህን መጣጥፍ ልናቀርብ የወደድነው::
ወያኔ እጅግ አድርጎ ከሚፈራው እና አጥብቆ ከሚጠላው ህዝባዊ ሃይል ዉስጥ አንዱ ወጣቱ ነው::ወጣቱ ሙሉ ነጻነትን እና ነጻ እንቅስቃሴን የሚናፍቅ ሃይል በመሆኑ ከአፋኙ የወያኔ አካሄድ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሲላተሙ እና ሲጋጩ ቆይተዋል::አንዳንዴ በድርጅት--ሌላ ጊዜ ደግሞ ማህበራዊ ክንውኖችን መሰረት አድርገው--ብዙ ጊዜም በየት/ቤቱ ዱላና ትንቅንቅ ማካሄዳቸው በታሪክ ተመዝግቦላቸዋል::ወያኔ ገና ጫካ እያለም ቢሆን ከጎንደር-ባህርዳር-የደሴ እና የደብረብርሃን ወጣቶች ጋር ፊት ለፊት የተጋፈጠ ሲሆን በየደረሰባቸው አካባቢወችም እየገደለ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም::
ወያኔ ሁዋላ ቀር የሆነ የፓለቲካኃይል ነው::17ቱን አመት የጫካ ህይወት ሲመሩ የቆዩት ጎጣቸዉን በሌሎች ጎጦች ላይ እንዴት በአስተማማኝ ሁኔታ መጫን እንደሚችሉ ዘዴ ሲዘይዱ ነበር::እንደምንም ብለው ስልጣን መያዝ ክቻሉ የፓለቲካ-የኢኮኖሚና -የባህል -ወታደራዊ የበላይነታቸዉን እንዴት እና በምን ስልት ማራመድ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት(sustainable) እንዲኖረው ማድረግ እንደሚችሉ ሲዳክሩ ነው የከረሙት::ወጣቱ ይህን አጥፊ አካሄድ እና ህልም ለመዋጋትም ጊዜ አልወሰደበትም::በደርግ ዉድቀት ማግስት በተለይ በ1983,1984,1985,1986 ወዘተ አመታት ወጣቱ በተለይም ምሁሩ ወጣት
ህይወትን የሚያስከፍል ብርቱ ትግል ማድረጋቸው የሚረሳ አይደለም::
በወያኔ እና በኢትዮጵያ ወጣት መካከል መሰረታዊ ቅራኔ አለ::ቅራኔው ከአንዱ ሁዋላቀርነትና ከሌላው ተራማጅ ባህርይ የሚመነጭ ነው::ወያኔ አሮጌ እና የበሰበሰ ባህል ያለው ጎታች እና አፋኝ ሃይል ነው::በአንጻሩ ወጣቱ ነጻነት-እድገት እና ተራማጅ እንዲሁም ዩኒቨርሳል የሆኑ ባህርያት ያሉት ትኩስ ሃይል ነው::እንግዲህ አሮጌ እና ጎታች ሃይል ከነጻው አዲስ ሃይል ጋር በምንም መንገድ ስምምነት ሊኖረው ካለመቻሉ በላይ ተጻራሪ ፍላጎት እና ህልም እንደሚኖራቸው መታወቅ አለበት::ወያኔ ይህ ሁኔታ ቁዋሚ ፍርሃት እና ጭንቀት ስለፈጠረበት አንዳንዴ በጥይት ሌላ ጊዜ ደግሞ በማምታታት ወጣቱን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ያልተቁዋረጠ ትግል አካሂዶዋል::ይህ የወያኔ ያልተቁዋረጠ ጥረትና ትግል እጂግ ብዙ መዋእለ-ንዋይ እና የሰው-ሃይል አስክፍሎታል::አሁንም ይህንን ጽሁፍ ስናዘጋጅ ወያኔ በወጣቱ መካከል ሰርጎ እየገባ የሚበትነው መዋእለ-ንዋይ መጠነሰፊ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል::
ወያኔ ወጣቱን በራሱ ድርጂት ስር ለማሰለፍ በርካታ ጥረቶችን ቢያደርግም በትምህርት ተቁዋማት አካባቢ የሚያደርገው ጥረት ግን እጂግ ወራዳው እና የዘቀጠው እንደሆነ በየጊዜው የምንሰማው ሁሉ ይመሰክራል::ለምሳሌ በዚህ አመት ብቻ በበርካታ የትምህርት ተቁዋማት ተማሪወችን የሚያፍን እና የሚጎዳ እርምጃወች የወሰዱ ሲሆን ዱላና ጥይትም በስፋት ተጠቅሞዋል::
ተማሪወችን በእምነታቸው ምክንያት ከትምህርት ቤት አባሮዋል::በምግብ ምክንያት የቀረብ ተቃውሞን መታገስ አቅቶዋቸው ተማሪወችን በቆመጥ እየደበደቡ አባረዋል::ለአባይ ግድብ አናዋጣም ያሉትንም አሳደዋል::የመማር-ማስተማሩን ስራ በሚመልከት የቀረበ ተቃውሞን እንደ አመጽ ቆጥረው በተማሪው ላይ እርምጃ ወስደዋል::የመለስን ራእይ በዩኒቨርስቲወች ለማሰራጨት በጠሩዋቸው ስብሰባወችም ዉግዘትና ተቃውሞ ደርሶባቸዋል::
በያዝነው የትምህርት አመት ወያኔ የመኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በስልጣን ላይ የመቀጠል ጉዳይ አስተማማኝ ለማድረግ ከወሰዳቸው በርካታ ዉሳኔወች ዋናው ወጣቱን በተለይም ተማሪዉን እና ምሁሩን ማዋከብ እና ማፈን በመሆኑ ገና አመቱ ሲጀምር አንድ ብሎ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪወች ጋር ነው የተፋለጠው::
በየትምህርት ቤቱና ተቁዋማቱ በሰገሰጋቸው ባንዳ ምሁራን እና "ቺስታ" ተማሪወች አማካኝነት የብዙሃኑን ተማሪ መብት ለማፈን እና እንቅስቃሴያቸዉንም ለመቆጣጠር መጠነሰፊ ብር ማፍሰስ ወሳኝ እንደሆነ ስለታመነበት ወያኔ እንደለመደው ብክነቱን ቀጥሎበታል::በዚህም አማካኝነት ተማሪዉን ለሁለት ከፍሎ አንዱን ወገን የቤት ልጅ--ሌላዉን ደግሞ ባይተዋር እና የ እንጀራ ልጅ በማድረግ ተማሪዉን እያመሰው ነው::
ታሪክን ወደሁዋላ መለስ ብለን በጥቂቱ ስንቃኝ የዚያ ዘመን ወጣት ለራሱ መብት ብቻ ሳይሆን ለመላው ሰፊ-ህዝብ መብቶች እንደተዋደቀ በዚህም አኩሪ የተጋድሎ ስራ እንደተመዘገበ አያጠራጥርም::የዚያ ዘመን ተማሪናወች ከሁሉ አስቀድሞ የግቢ ነጻነቶችን (campus freedoms) ለመቀዳጀት የተከተላቸው ስልቶች እና የከፈላቸው መስዋእትነት የሚያኮሩም ስኬታማም ነበሩ::በካምፓስ ዉስጥ መጠነሰፊ ዉይይቶች ለማካሄድ እና በነጻነትም የተማሪ ምክርቤቶችን(student counsels) ለማቁዋቁዋም የተደረጉ ጥረቶች አስደናቂ ነበሩ::እነዚያን የተማሪ ማህበራት ማቁዋቁዋም ብቻ ሳይሆን በሁሉም መንገድ አጠናክሮ የራሱን የተማሪዉን እና የመላ ህብረተሰቡን መሰረታዊ ጥያቄወች ለማስተጋባት የተደርጉት መራራ ትግሎች አንጸባራቂ ነበሩ::ለቀጣዩም ትውልድ የመማርያ መጻህፍት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው::
ዛሬ ወያኔ ከአጼዉም ሆነ ከደርጉ በባሰ ሁኔታ አፋኝ-ገዳይ-ነፍሰ በላ መሆኑን መጠራጠር ትክክል አይደለም::ተማሪዉን እና ወጣቱን በዘር የከፋፈለ ወያኔ ነው::በዘር ከፋፍሎም ወጣቱን ያፋጀ ወያኔ ነው::የትምህርትን ጥራት በማበላሸት የወጣቱን የማወቅ እና የብስለት ደርጃ ያዋረደ ወያኔ ነው::ስለዚህም ወያን እና ወጣቱ እሳትና ጭድ ናቸው ብለን ማመን ተገቢ ይሆናል::
ዛሬ ከወያኔ ባላነሰ ወጣቱን የጎዱ እና በመጉዳት ላይ ያሉ "ተቃዋሚ" ተብየወችም አሉ::ስለወጣቱ ትክክለኛ ፓሊሲ ካለመከተላቸው በላይ ወያኔንም አስመልክቶ የሚቀይሱት ስልት ሁሉ ደካማ በመሆኑ የወጣቱን ትግል አዳክመዉታል::ጥቂት የማይባሉ "ተቃዋሚ" ተብየወች ወጣቱን ለኪራይ ሰብሳቢነት ምኞታቸው ፊዳ ከማድረጋቸው ሌላ ስለሃገሪቱ መሰረታዊ ችግሮች እና መፍትሄወችም ሸዉራራ አመለካከት እንዲኖረዉና ወዳጅ-ጠላቱንም እንዳይለይ በማድረግ አዳክመዉታል::
የያዝነው አመት በወያኔ እና በወጣቱ መካከል ያለው ቅራኔ የጦዘበት ነው::ወያኔ በአለም ዋንጫ አሳቦ በ"ዋልያ" ስም ቡራቡሬ ማልያ እያውለበለበ ወጣቱን ሊያዘናጋ ሞክሮዋል::ባይሳካለትም::ሌላው ቅራኔ የእምነት ነጻነትን የሚጠይቁ ወጣቶች መበራከት ሲሆን በርካታ እናቶች እና አባቶች የትግሉ አካል ሆነዋል::እዚህ ላይ የማንዘርዝዝራቸው በርካታ እሳቶች እዚህ እና እዚያ እየተለኮሱ ሲሆን ድንጋይ ወርዋሪ ወጣቶች እና አድማ ፈልፋዩ ወያኔ በዚህ በሚጦዘው እሳት ዉስጥ በአሸናፊና ተሸናፊ መጠናቀቅ ያለበት ጉዳይ እንዳላቸው መታወቅ አለበት::
የትላንት አበው ታጋዮች ደግመው ደጋግመው እንዳሉት:---
አንተ ተሰዋና ልጅህ ሞትን ይማር
እንዳይሆን ከፈለግህ የልጅ ልጅ ገባር!!!!
የሰሞኑ የሳውዲ አራብያ መንግስት እጅግ አሰቃቂ እርምጃወች ይህንኑ ሃቅ ያንጸባርቃሉ::የሳውዲ መግስት ህገወጥ ነው የሚለዉን በህገወጥ መንገድ አሻሽሎ እየፈጸመው ሲሆን የአለም ሰብ አዊ መብት ተሙዋጋቾችም አውግዘዉታል-ድርጊቱንም ኮንነዉታል:: ይሁን እንጂ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ድርጊቱ እንደ ብሄራዊ ዉርደት ቆጥረን በያለንበት በአደባባይ ቁጣችንን እና ተቃውሞዋቺንን ለማሰማት መቻላቺን ታላቅ ገድልም-ድልም ነው::ዜጎቻችን በደረሰባቸው ጥቃት ላይ መነሻ አድርገን ያሳየነዉን ህብረት በችግሩ ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይም ይበልጥ ሃያል እና ብርቱ ማድረግ ይጠበቅብናል::
ከሳዉዲ የታፈሱ -በቆመጥ የተደበደቡትና በካራ የተሸለቱት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ተማሪወችም እጂግ ብዙ ቁጥር አላቸው::ጥቂት የማይባሉ የደርግን ግፈኛ አገዛዝ እና የወያኔም ዘረኛ ስር አት በመቃወም ወይም በመሸሽ የተሰደዱ ብዙዎች ናቸው:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ወጣት ሴቶችን በስራ አሳቦ ጉልበታቸዉን ሊመዘብር ለአረብ ሃገራት የተሸጣቸው እህቶች የወያኔ ቆሻሻ ፓሊስ ሰለባወች ናቸው::የፓለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ስደተኛ ብለን መክፈል ታላቅ ሃጢአት ይሆናል::ሁሉም ማለት ይቻላል የወያኔ የግፍ አገዛ ሰለባወች ናቸው::እዚህ ላይ ነው ከላይ የሰፈረው ስንኝ ፓለቲካዊ ፋይዳዉና ጥቅሙ የሚጎላው::ለነጻነት ሁሉንም አይነት መስዋእት መክፈል እጂግ አስፈላጊ እንጂ ፈራ ተባ የሚባልበት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባናል::::
የዘመኑ ወጣት እንደአያት ቅድመአያቶቹ ለአንድነት እና ለአርበኘነት እራሱን ዝግጁ አድርጎ ማቅረብ የሚጠበቅበት ቢሆንም የትምህርት ተቁዋማትን ግን አስቀድሞ በመቆጣጠር የራሱን ነጻነት ማወጅ ቁጥር አንድ ሃላፊነቱ ነው ::የመማርያ ግቢዉን በወያኔ ፌዴራል ያስደፈረ ተማሪ የአገር አንድነት ላይ ጠንካራ አቁዋም ይኖረዋል ተብሎ ማመን አይቻልም::ወያኔንም ሆነ ፌዴራል ፓሊስን እንዲሁም በሊግ ስም የተሰገሰጉ ሰላይ "ተማሪወችን" በመመንጠር ተማሪዉና መህራን ግቢያቸዉን(campus) በማጽዳት ህብረብሄራዊ እና ሃገር አቀፍ ዴሞክራሲያው ትግሉን ማቀጣጠል ይጠበቅባቸዋል:: ምክንያቱም የነጻነት ትግሉ ከትምህርት ተቁዋማት ግቢ ይጀምራልና!!!ወያኔን በትምህርት ቅጥር ግቢወች ዉስጥ ድባቅ የመታ ወጣትና ምሁር ለኢትዮጵያ አንድነትና ለህዝቡዋ ነጻነት አስተማማኝ ሃይል ነው::ይህን ማድረግ ስንችል ነው በወያኔ ላይ ድል መቀዳጀት የምንችለው::ስለዚህም ተቃዋሚ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች የኪራይ ሰብሳቢወችን ጥረት እያከሽፉ ተማሪው በመማርያ ግቢው ዉስጥ ነጻነቱን እንዲቀዳጅ ማስቻል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባር መሆኑን ልናውቅ ይገባል::
ወያኔ ተማሪዉን ለማሽመድመድ ያስቻሉት እና እንደስኬት ከሚቆጥራቸው አንዱ መምህራንን በትምህርት ተቁዋማት ዉስጥ ገለልተኛ ማድረግ መቻሉ ነው:: ይህም ጥረቱ ለጥቂት አመታት የተሳካለት ይመስላል::ለምሳሌ በዚህ ምክንያት ተማሪዉና መምህራኑ በስርአቱ ላይ የጋራ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችላቸዉን የተቃውሞ ግንባር እና ሶሊዳሪቲ አልመሰረቱም::የተማሪወች ምክርቤቶች በነጻነት አይሰሩም::ወይም በወያኔ ሊጎች ቁጥጥር ስር ናቸው::ተማሪወች እጂግ አናሳዉን እና መሰረታዊዉን ሃሳብን በነጻነት በግቢያቸው ዉስጥ የመግለጽ መብታቸዉን አላስከበሩም::መምህራንም ገለልተኛ ወይም ባይተዋር በመሆናቸው ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በዘመነ ወያኔ ሊዋደቁለት የሚገባ ስብ አዊ መብት አይደለም ብለው ደምድመዋል::ምናልባትም የአካዳሚክ ነጻነት ዋናው መሰረቱ FREEDOM OF EXPRESSION መሆኑን ወርቀት በትነን ልናስተምራቸው ይገባል::
አድማ ፈልፋዩ ወያኔና አድማ ፈልፋዩ ፓሊሲያቸው እስካለ ድረስ ድንጋይ ወርዋሪና ታጋይ መምህራን ብቅ ማለታቸው አይቀሬ ነው::እናም ተሜ ቢያንስ ለግቢያቸው ሙሉ ነጻነት መዋቅደቅ ተገቢ ነው ብለን ማመን እና መነሳት አለብን::
ከወያኔ በነጻ የሚሰጥ መብት እና ነጻነት የለም::የመብት ሸርፍራፊወችም ሊያዘናጉን አይገባም::የመለስ ራእይ የሚባለዉም የዛገ ምላጭ በመሆኑ አደገኛ ነው::አሳምረን በጽናት ልንታገለው ብሎም ልናሸንፈው የሚገባ ጎታች እና አድሃሪ አስተሳሰብ ነው::የመለስ ራእይ ዘረኝነት-ጎጠኝነት ሲሆን ጎታች እና ጨለምተኛ ነው::በድንጋይም በብእርም ልንዋጋውና ልናሸንፈው ይገባል እንላለን::
ተማሪወች-በወያኔ ላይ ድንጋይ ወርውሩ!!!!
ወጣቶች ትምህርት ተቁዋማትን ከወያኔ ነጻ አውጡ!!!
No comments:
Post a Comment