Friday, 22 November 2013

ድንጋይ ወርዋሪ ተማሪወች -ታጋይ መምህራንና-አድማ ፈልፋዩ ወያኔ በ2006.



                       ሕወሃት /ወያኔ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወጥቶ መሃል አገር የፈነዳ ትኩስ "ዴሞክራት" በመሆኑ የማይችለበትን እና የማያውቅበትን የሃገር እና የህዝብ አስተዳደር ቀዉስ ዉስጥ እንደጣለው በገሃድ የታየ ነው::የጎጥ መርሆዎቹን ከአገራዊ ፍላጎቶች ጋር--አገራዊ ፍላጎቶቹን ደግሞ ከአለም አቀፋዊ ጉዳዮች ጋር ማጋመድ ስላልቻለበት ላለፉት ሃያ መናምን አመታት አገሪቱን የእዉር የድንብሩን ሲያተራምሳት እንጂ  በወጉ ሲያስተዳድራት አልነበረም::

                    ወያኔ መነሻዉና መንደርደርያው ጎጡ  እና ጎጡ ብቻ ስለሆነ የተቃና ሁሉን አቀፍ የህዝብ አስተዳደር እና አመራር ፓሊሲ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ነው::ባገሪቱ ነባር ባህላዊ መዋቅሮችም ይሁን እነሱው በጠፈጠፉዋቸው መዋቅራት ዉስጥ አለም ያወቃቸዉን የአስተዳደር ስርአቶችን ወድጎን በመግፋት ወታደራዊ ስልቶችን በሲቭል መስርያቤቶች ሳይቀር ተጠቅመዋል::

                ወያኔ ህዝቡን በረዥም ታሪኩ ባዳበረዉና  እና ባበለጸጋቸው የአስተዳደር ዘዴወች መምራትእንዳልቻሉበትና ይልቁንስ ደግሞ ደጋግሞ ከህዝብ ጋር እየተጋጩ እንደሆነ በርካታ ማስረጃወችን መደርደር ይቻላል::በደቡብ ያገሪቱ ክልሎች የራሱን ህገመንግስት ጥሶ የአናሳ ብሄር ብሄርሰቦችን መብት እና ህልዉና ሲጨፈልቅ እንደነበር በ2004/5 በሪፓርት ተመዝግቦ አንብበናል:በ አለም አቀፍ የዜና አውታሮች እና ሰብ አዊ መብት ተንከባባካቢ ወገኖችም አማካኝነት አለም እንዲሰማው ተደርጎዋል::::

                እንዲያው ለመነሻ ያህል ወያኔና የህዝብ አገልግሎት ፓሊሲወች ጭራሽ እንደማይተዋወቁ --በዚህም ሳብያ ማህበረሰቡ በበርካታ ወያኔ ሰራሽ ቀውሶችና ውጥረቶች የተቀፈደደ መሆኑን ከጠቆምን በሁዋላ  በያመቱ ከወጣቱ ጋር የሚያደርገው  ትንቅንቅ ዘንድሮ ምን ሊመስል ይችላል:-ወጣቱስ ምን ምርጫ አለው በማለት በጥቂቱ ለመዳሰስ ነው ይህን መጣጥፍ ልናቀርብ የወደድነው::

              ወያኔ እጅግ አድርጎ ከሚፈራው እና አጥብቆ ከሚጠላው ህዝባዊ ሃይል ዉስጥ አንዱ ወጣቱ ነው::ወጣቱ ሙሉ ነጻነትን እና ነጻ እንቅስቃሴን የሚናፍቅ ሃይል በመሆኑ ከአፋኙ የወያኔ አካሄድ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሲላተሙ እና ሲጋጩ ቆይተዋል::አንዳንዴ በድርጅት--ሌላ ጊዜ ደግሞ ማህበራዊ ክንውኖችን መሰረት አድርገው--ብዙ ጊዜም በየት/ቤቱ ዱላና ትንቅንቅ ማካሄዳቸው በታሪክ ተመዝግቦላቸዋል::ወያኔ ገና ጫካ እያለም ቢሆን ከጎንደር-ባህርዳር-የደሴ እና የደብረብርሃን ወጣቶች ጋር ፊት ለፊት የተጋፈጠ ሲሆን በየደረሰባቸው አካባቢወችም እየገደለ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም::

              ወያኔ ሁዋላ ቀር የሆነ የፓለቲካኃይል ነው::17ቱን አመት የጫካ ህይወት ሲመሩ የቆዩት ጎጣቸዉን በሌሎች ጎጦች ላይ እንዴት በአስተማማኝ ሁኔታ መጫን እንደሚችሉ ዘዴ ሲዘይዱ ነበር::እንደምንም ብለው ስልጣን መያዝ ክቻሉ የፓለቲካ-የኢኮኖሚና -የባህል -ወታደራዊ የበላይነታቸዉን እንዴት እና በምን ስልት ማራመድ ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት(sustainable) እንዲኖረው ማድረግ እንደሚችሉ ሲዳክሩ ነው  የከረሙት::ወጣቱ ይህን አጥፊ አካሄድ እና ህልም ለመዋጋትም ጊዜ አልወሰደበትም::በደርግ ዉድቀት ማግስት በተለይ በ1983,1984,1985,1986 ወዘተ አመታት ወጣቱ በተለይም ምሁሩ ወጣት
ህይወትን የሚያስከፍል ብርቱ ትግል ማድረጋቸው የሚረሳ አይደለም::

             በወያኔ እና በኢትዮጵያ ወጣት መካከል መሰረታዊ ቅራኔ አለ::ቅራኔው ከአንዱ ሁዋላቀርነትና ከሌላው ተራማጅ ባህርይ የሚመነጭ ነው::ወያኔ አሮጌ እና የበሰበሰ ባህል ያለው ጎታች እና አፋኝ ሃይል ነው::በአንጻሩ ወጣቱ ነጻነት-እድገት እና ተራማጅ እንዲሁም ዩኒቨርሳል የሆኑ ባህርያት ያሉት ትኩስ ሃይል ነው::እንግዲህ አሮጌ እና ጎታች ሃይል ከነጻው አዲስ ሃይል ጋር በምንም መንገድ ስምምነት ሊኖረው ካለመቻሉ በላይ ተጻራሪ ፍላጎት እና ህልም እንደሚኖራቸው መታወቅ አለበት::ወያኔ ይህ ሁኔታ ቁዋሚ ፍርሃት እና ጭንቀት ስለፈጠረበት አንዳንዴ በጥይት ሌላ ጊዜ ደግሞ በማምታታት ወጣቱን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ያልተቁዋረጠ ትግል አካሂዶዋል::ይህ የወያኔ ያልተቁዋረጠ ጥረትና ትግል እጂግ ብዙ መዋእለ-ንዋይ እና የሰው-ሃይል አስክፍሎታል::አሁንም ይህንን ጽሁፍ ስናዘጋጅ ወያኔ በወጣቱ መካከል ሰርጎ እየገባ የሚበትነው መዋእለ-ንዋይ መጠነሰፊ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል::


              ወያኔ ወጣቱን በራሱ ድርጂት ስር ለማሰለፍ በርካታ ጥረቶችን ቢያደርግም በትምህርት ተቁዋማት አካባቢ የሚያደርገው ጥረት ግን እጂግ ወራዳው እና የዘቀጠው እንደሆነ በየጊዜው የምንሰማው ሁሉ ይመሰክራል::ለምሳሌ በዚህ አመት ብቻ በበርካታ የትምህርት ተቁዋማት ተማሪወችን የሚያፍን እና የሚጎዳ እርምጃወች የወሰዱ ሲሆን ዱላና ጥይትም በስፋት ተጠቅሞዋል::

            ተማሪወችን በእምነታቸው ምክንያት ከትምህርት ቤት አባሮዋል::በምግብ ምክንያት የቀረብ ተቃውሞን መታገስ አቅቶዋቸው ተማሪወችን በቆመጥ እየደበደቡ አባረዋል::ለአባይ ግድብ አናዋጣም ያሉትንም አሳደዋል::የመማር-ማስተማሩን ስራ በሚመልከት የቀረበ ተቃውሞን እንደ አመጽ ቆጥረው በተማሪው ላይ እርምጃ ወስደዋል::የመለስን ራእይ በዩኒቨርስቲወች ለማሰራጨት በጠሩዋቸው ስብሰባወችም ዉግዘትና ተቃውሞ ደርሶባቸዋል::

             በያዝነው የትምህርት አመት ወያኔ የመኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በስልጣን ላይ የመቀጠል ጉዳይ አስተማማኝ ለማድረግ ከወሰዳቸው በርካታ ዉሳኔወች ዋናው ወጣቱን በተለይም ተማሪዉን እና ምሁሩን ማዋከብ እና ማፈን በመሆኑ ገና አመቱ ሲጀምር አንድ ብሎ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪወች ጋር ነው የተፋለጠው::

               በየትምህርት ቤቱና ተቁዋማቱ በሰገሰጋቸው ባንዳ ምሁራን እና "ቺስታ" ተማሪወች አማካኝነት የብዙሃኑን ተማሪ መብት  ለማፈን እና እንቅስቃሴያቸዉንም ለመቆጣጠር መጠነሰፊ ብር ማፍሰስ ወሳኝ እንደሆነ ስለታመነበት ወያኔ እንደለመደው ብክነቱን ቀጥሎበታል::በዚህም አማካኝነት ተማሪዉን ለሁለት ከፍሎ አንዱን ወገን የቤት ልጅ--ሌላዉን ደግሞ ባይተዋር እና የ እንጀራ ልጅ በማድረግ ተማሪዉን እያመሰው ነው::

              ታሪክን ወደሁዋላ መለስ ብለን በጥቂቱ ስንቃኝ የዚያ ዘመን ወጣት ለራሱ መብት ብቻ ሳይሆን ለመላው ሰፊ-ህዝብ መብቶች እንደተዋደቀ በዚህም አኩሪ የተጋድሎ ስራ እንደተመዘገበ አያጠራጥርም::የዚያ ዘመን ተማሪናወች ከሁሉ አስቀድሞ የግቢ ነጻነቶችን (campus freedoms) ለመቀዳጀት  የተከተላቸው ስልቶች እና የከፈላቸው መስዋእትነት የሚያኮሩም ስኬታማም ነበሩ::በካምፓስ ዉስጥ መጠነሰፊ ዉይይቶች ለማካሄድ እና በነጻነትም የተማሪ ምክርቤቶችን(student counsels) ለማቁዋቁዋም የተደረጉ ጥረቶች አስደናቂ ነበሩ::እነዚያን የተማሪ ማህበራት ማቁዋቁዋም ብቻ ሳይሆን በሁሉም መንገድ አጠናክሮ የራሱን የተማሪዉን እና የመላ ህብረተሰቡን መሰረታዊ ጥያቄወች ለማስተጋባት የተደርጉት መራራ ትግሎች አንጸባራቂ ነበሩ::ለቀጣዩም ትውልድ የመማርያ መጻህፍት ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው::

                ዛሬ ወያኔ ከአጼዉም ሆነ ከደርጉ በባሰ ሁኔታ አፋኝ-ገዳይ-ነፍሰ በላ መሆኑን መጠራጠር ትክክል አይደለም::ተማሪዉን እና ወጣቱን በዘር የከፋፈለ ወያኔ ነው::በዘር ከፋፍሎም ወጣቱን ያፋጀ ወያኔ ነው::የትምህርትን ጥራት በማበላሸት የወጣቱን የማወቅ እና የብስለት ደርጃ ያዋረደ ወያኔ ነው::ስለዚህም ወያን እና ወጣቱ እሳትና ጭድ ናቸው ብለን ማመን ተገቢ ይሆናል::

            ዛሬ ከወያኔ ባላነሰ ወጣቱን የጎዱ እና በመጉዳት ላይ ያሉ "ተቃዋሚ" ተብየወችም አሉ::ስለወጣቱ ትክክለኛ ፓሊሲ ካለመከተላቸው በላይ ወያኔንም አስመልክቶ የሚቀይሱት ስልት ሁሉ ደካማ በመሆኑ የወጣቱን ትግል አዳክመዉታል::ጥቂት የማይባሉ "ተቃዋሚ" ተብየወች ወጣቱን ለኪራይ ሰብሳቢነት ምኞታቸው ፊዳ ከማድረጋቸው ሌላ ስለሃገሪቱ መሰረታዊ ችግሮች እና መፍትሄወችም ሸዉራራ አመለካከት እንዲኖረዉና ወዳጅ-ጠላቱንም እንዳይለይ በማድረግ አዳክመዉታል::

            የያዝነው አመት በወያኔ እና በወጣቱ መካከል ያለው ቅራኔ የጦዘበት ነው::ወያኔ በአለም ዋንጫ አሳቦ በ"ዋልያ" ስም ቡራቡሬ ማልያ እያውለበለበ ወጣቱን ሊያዘናጋ ሞክሮዋል::ባይሳካለትም::ሌላው ቅራኔ የእምነት ነጻነትን የሚጠይቁ ወጣቶች መበራከት ሲሆን በርካታ እናቶች እና አባቶች የትግሉ አካል ሆነዋል::እዚህ ላይ የማንዘርዝዝራቸው በርካታ እሳቶች እዚህ እና እዚያ እየተለኮሱ ሲሆን ድንጋይ ወርዋሪ ወጣቶች እና አድማ ፈልፋዩ ወያኔ በዚህ በሚጦዘው እሳት ዉስጥ በአሸናፊና ተሸናፊ መጠናቀቅ ያለበት ጉዳይ እንዳላቸው መታወቅ አለበት:: 

               የትላንት አበው ታጋዮች ደግመው ደጋግመው እንዳሉት:---
               አንተ ተሰዋና ልጅህ ሞትን ይማር
               እንዳይሆን ከፈለግህ የልጅ ልጅ ገባር!!!!
የሰሞኑ የሳውዲ አራብያ መንግስት እጅግ አሰቃቂ እርምጃወች ይህንኑ ሃቅ ያንጸባርቃሉ::የሳውዲ መግስት ህገወጥ ነው የሚለዉን በህገወጥ መንገድ አሻሽሎ እየፈጸመው ሲሆን የአለም ሰብ አዊ መብት ተሙዋጋቾችም  አውግዘዉታል-ድርጊቱንም ኮንነዉታል:: ይሁን እንጂ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ድርጊቱ እንደ ብሄራዊ ዉርደት ቆጥረን በያለንበት በአደባባይ ቁጣችንን እና ተቃውሞዋቺንን ለማሰማት መቻላቺን ታላቅ ገድልም-ድልም ነው::ዜጎቻችን በደረሰባቸው ጥቃት ላይ መነሻ አድርገን ያሳየነዉን ህብረት በችግሩ ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይም ይበልጥ ሃያል እና ብርቱ ማድረግ ይጠበቅብናል::

               ከሳዉዲ የታፈሱ -በቆመጥ የተደበደቡትና በካራ የተሸለቱት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ ተማሪወችም እጂግ ብዙ ቁጥር አላቸው::ጥቂት የማይባሉ የደርግን ግፈኛ አገዛዝ እና የወያኔም ዘረኛ ስር አት በመቃወም ወይም በመሸሽ የተሰደዱ ብዙዎች ናቸው:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ወጣት ሴቶችን በስራ አሳቦ ጉልበታቸዉን ሊመዘብር ለአረብ ሃገራት የተሸጣቸው እህቶች የወያኔ ቆሻሻ ፓሊስ ሰለባወች ናቸው::የፓለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ስደተኛ ብለን መክፈል ታላቅ ሃጢአት ይሆናል::ሁሉም ማለት ይቻላል የወያኔ የግፍ አገዛ ሰለባወች ናቸው::እዚህ ላይ ነው ከላይ የሰፈረው ስንኝ ፓለቲካዊ ፋይዳዉና ጥቅሙ የሚጎላው::ለነጻነት ሁሉንም አይነት መስዋእት መክፈል እጂግ አስፈላጊ እንጂ ፈራ ተባ የሚባልበት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባናል::::

           የዘመኑ ወጣት እንደአያት ቅድመአያቶቹ ለአንድነት እና ለአርበኘነት እራሱን ዝግጁ አድርጎ ማቅረብ የሚጠበቅበት ቢሆንም የትምህርት ተቁዋማትን ግን አስቀድሞ በመቆጣጠር የራሱን ነጻነት ማወጅ ቁጥር አንድ ሃላፊነቱ ነው ::የመማርያ ግቢዉን በወያኔ ፌዴራል ያስደፈረ ተማሪ የአገር አንድነት ላይ ጠንካራ አቁዋም ይኖረዋል ተብሎ ማመን አይቻልም::ወያኔንም ሆነ ፌዴራል ፓሊስን እንዲሁም በሊግ ስም የተሰገሰጉ ሰላይ "ተማሪወችን" በመመንጠር ተማሪዉና መህራን ግቢያቸዉን(campus) በማጽዳት ህብረብሄራዊ እና ሃገር አቀፍ ዴሞክራሲያው ትግሉን ማቀጣጠል ይጠበቅባቸዋል:: ምክንያቱም የነጻነት ትግሉ ከትምህርት ተቁዋማት ግቢ ይጀምራልና!!!ወያኔን በትምህርት ቅጥር ግቢወች ዉስጥ ድባቅ የመታ ወጣትና ምሁር ለኢትዮጵያ አንድነትና ለህዝቡዋ ነጻነት አስተማማኝ ሃይል ነው::ይህን ማድረግ ስንችል ነው በወያኔ ላይ ድል መቀዳጀት የምንችለው::ስለዚህም ተቃዋሚ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች የኪራይ ሰብሳቢወችን ጥረት እያከሽፉ ተማሪው በመማርያ ግቢው ዉስጥ ነጻነቱን እንዲቀዳጅ ማስቻል የወቅቱ አጣዳፊ ተግባር መሆኑን ልናውቅ ይገባል::

             ወያኔ ተማሪዉን ለማሽመድመድ ያስቻሉት እና እንደስኬት ከሚቆጥራቸው አንዱ መምህራንን በትምህርት ተቁዋማት ዉስጥ ገለልተኛ ማድረግ መቻሉ ነው:: ይህም ጥረቱ ለጥቂት አመታት የተሳካለት ይመስላል::ለምሳሌ  በዚህ ምክንያት ተማሪዉና መምህራኑ በስርአቱ ላይ የጋራ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችላቸዉን የተቃውሞ ግንባር እና ሶሊዳሪቲ አልመሰረቱም::የተማሪወች ምክርቤቶች በነጻነት አይሰሩም::ወይም በወያኔ ሊጎች ቁጥጥር ስር ናቸው::ተማሪወች እጂግ አናሳዉን እና መሰረታዊዉን ሃሳብን በነጻነት በግቢያቸው ዉስጥ የመግለጽ መብታቸዉን አላስከበሩም::መምህራንም ገለልተኛ ወይም ባይተዋር በመሆናቸው ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በዘመነ ወያኔ ሊዋደቁለት የሚገባ ስብ አዊ መብት አይደለም ብለው ደምድመዋል::ምናልባትም  የአካዳሚክ ነጻነት ዋናው መሰረቱ FREEDOM OF EXPRESSION መሆኑን ወርቀት በትነን ልናስተምራቸው ይገባል::

             አድማ ፈልፋዩ ወያኔና አድማ ፈልፋዩ ፓሊሲያቸው እስካለ ድረስ ድንጋይ ወርዋሪና ታጋይ መምህራን ብቅ ማለታቸው አይቀሬ ነው::እናም ተሜ ቢያንስ ለግቢያቸው ሙሉ ነጻነት መዋቅደቅ ተገቢ ነው ብለን ማመን እና መነሳት አለብን::
ከወያኔ በነጻ የሚሰጥ መብት እና ነጻነት የለም::የመብት ሸርፍራፊወችም ሊያዘናጉን አይገባም::የመለስ ራእይ የሚባለዉም የዛገ ምላጭ በመሆኑ አደገኛ ነው::አሳምረን በጽናት ልንታገለው ብሎም ልናሸንፈው የሚገባ ጎታች እና አድሃሪ አስተሳሰብ ነው::የመለስ ራእይ ዘረኝነት-ጎጠኝነት ሲሆን ጎታች እና ጨለምተኛ ነው::በድንጋይም በብእርም ልንዋጋውና ልናሸንፈው ይገባል እንላለን::




ተማሪወች-በወያኔ ላይ ድንጋይ ወርውሩ!!!!
ወጣቶች ትምህርት ተቁዋማትን ከወያኔ ነጻ አውጡ!!!

          

             
 


Tuesday, 17 September 2013

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃላፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ


    አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ 94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የ12 ሚሊዮን ብር እና የ34 ሚሊዮን ብር ህገወጥ ብድርን እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት በቂ የሰነድ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ቢገለጽም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቱዋል፡፡
በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከመመሪያና አሰራር ውጪ ለግለሰቦች የስልክ መስመር እንዲዘረጋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ስልክ በማስደወል በመስሪያ ቤቱ ላይ 14 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱን የተመለከተ ሁለት ምርመራዎች ተጠናቀው በክስ ሂደት ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሚፈጥሩት ጫና ክሱ እየተጓተተ ነው።
በትግራይ ክልል የሚገኘው በሼባ የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ መብራት ሀይል ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ 65 ሚሊዮን 300 ሺ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጣርቶ ለወሳኝ አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
በተመሳሳይ በኦሮምያ ክልል በደብረዘይት የሚገኝ የግል የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረሱ ምርመራው አጣርቶ የፀረ ሙስና ኮሚሺን ቢልክም የፍትህ መጓተት ታይቶበታል።
በመብራት ሀይል አላግባብ በ 248 ሚሊዮን 900 ሺ ብር የተፈጸመ የ4 ሺ4 መቶ 70 ትራንስፎርመሮች አለም አቀፍ ግዢ በሁለት የምርመራ መዝገቦች የተጣራ ቢሆንም ውሳኔ አልተሰጠበትም።
ንብረቱ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኑፋክቸሪንግ ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የሆነ ግምቱ 4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ የብርና የነሃስ ሜዳልያ ከግምጃ ቤት በመጥፋቱ ተመርምሮ የተረጋገጠ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
በተንዳሆ ፕሮጀክት ከግብር ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ተመስርቷል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሊዝ እንዲስተናገድ የተወሰነለትን የመኖሪያ ቤት ኅ/ሥ/ማ ያለ ሊዝ በማስተናገድ የተሰጠ 30 ሺ 3 መቶ 32 ካ/ሜ ቦታ ምርመራ ተጠናቆ ክስ የተመሰረተ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
ለብሄራዊ ባንክ በሽያጭ ከሚቀርብ ወርቅ ጋር በተያያዘ የባንኩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች በመመሳጠር 63 ሚሊዮን ብር በመመዝበር አስቀድሞ ተከሰው የነበሩ አሁን ጥፋተኛ ተብለው ጉዳዩ ለቅጣት ውሳኔ ተቀጥሯል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ በልማት ተነሺዎች ስም ከመመሪያ ውጪ ግምቱ 13 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ የሆነ 2, ሺ 1 መቶ 45 ካ/ሜትር ትርፍ መሬት አላግባብ በተሰጣቸው እና ከካሳ ክፍያም ጋር በተያያዘ 5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር በትርፍ የተከፈላቸው ግለሰቦች ጉዳይ፤ በኢትዮጵያ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሀዋሳ ቅርንጫፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሃኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተደረገ የ100 ሚሊዮን የእህል ግዢ ጨረታ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑ በተደረገው ምርመራ በመረጋገጡ ጨረታው እንዲሰረዝና በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት የተደረገባቸው በጥቅሉ ከህዝብ በግብር የተሰበሰበ በርካታ ገንዘብ በአንድም በሌላ መልኩ በከፍተኛ አመራሮች ተጽእኖ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ተጣርቶ ለፍርድ ሰጭው አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ቀርተዋል፡፡
ከ 7 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የመዘበሩ የስራ ሃፊዎች አልተቀጡም ሲል ከፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ አሀዙ በ2005 የተፈጸመውን ሙስና አላካተተም።
ባለፉት 22 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት የተፈጸሙና በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተጣራ በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ይገመታል።

ምንጭ:-
posted by Aseged Tamenе